የከተማ አስተዳደራችን ቁልፍ ተግባር ተቋም መገንባት ነው !
ዛሬ በተቋማት ከምንሰራቸው የሪፎርም ስራዎች በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተቋም ግንባታ እና የሰው ሃይል ልማት በ10 ዙር ሲሰለጥኑ የነበሩ ኦፊሰሮችን አስመርቀናል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው፣ ኦፊሰሮቻችን ከህዝብ ጋር አክብሮት የተሞላበት ተግባቦት እንዲኖራቸው፣ ህግና ስርዓትን ያለአንዳች አድልዎ እንዲያስከብሩ፣ ፍፁም አገልጋይነት እንዲላበሱ ፣ ስነምግባር የተላበሱ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።
የደንብ ማስከበር አፊሰሮቻችን ስታገለግሉ ህዝባችሁን በፍቅር፣ በትህትና እና በማክበር እንዲሁም የወጡ ደንቦችን የለምንም ርህራሄና ያለአድልዎ በማስከበረ እንዲሆን ይጠበቅባችኋል ።
ተቋሞቻችን በስርዓት የተገነቡ፣ ጠንካራ የአገልግሎት ስርዓት ያላቸው፤ ስነምግባር የተላበሱና አገልጋይ እንዲሁም ለህዝብ ቅርብ የሆኑ ባለሙያ እና አመራር የመፍጠር ተቋማዊ የሪፎርም ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ከተማችን የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆኗ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ወታደራዊ አለባበስ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ እንዲሆን ሲጠቀሙበት ከነበረው የደንብ ልብስ ተጨማሪ ሆኖ የሚያገለግል አዲስ የደንብ ልብስ ይፋ አድርገናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.