የትውልድ ግንባታ ዙሪያ እየሰራን ካለነው ስራ ልምድ ለመቅሰም የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች እና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የመጡ እንግዶችን ዛሬ ተቀብለናል::
አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ ግልፅ ራዕይ አስቀምጠን በዚያ ላይ በመመርኮዝ እስከ 2018 ድረስ ምንም ገቢ የሌላቸው 1.3 ሚሊዮን ሁሉን አቀፍ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያገኙ ህጻናትን እና 330 ሺ የሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶችና ህጻናትን ማዕከል ያደረገ የተመጣጠነ ምግብ ፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የስነ ልቦና ግንባታ ቀጥታ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ እንገኛለን::
ይህ የትውልድ ግንባታ ስራችን የሚተገበረው ከጽንስ ጀምሮ እስከ ስድስት ዓመት ባሉ ህጻናት ላይ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ለእናቶች የምክር አገልግሎት የሚሰጡ 5000 ባለሞያዎችን አሰልጥነን ወደ ስራ ያስገባን ሲሆን 4000 የሚሆኑ መምህራንን በቅድመ መደበኛ ሙያ በማሰልጠን ወደ ተግባር እንዲገቡ አድርገናል::
እስከ አሁን በተገኘ ውጤት ለሕጻናት ጤና አገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ የጤና ተቋማትን ማሸጋገር፣ መምህራንን በማሰልጠን ሕጻናትን በጨዋታ እንዲያስተምሩ ማድረግ ፣ ከ597 በላይ የህጻናት መዋያ ቦታዎችን በግልና በመንግስት ተቋማት መገንባት ፣ ለልጆች መጫወቻ እንዲውሉ 305 መጫወቻ ስፍራዎች ግንባታ ማከናወን እና 114 መንገዶችን በመለየትና ዝግ እንዲሆኑ በማድረግ ለከተማችን ህጻናት ግልጋሎት እንዲውሉ አድርገናል::
አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ እንዲሁም ወላጆችና አሳዳጊዎች በእውቀት ልጆቻቸውን አሳድገው ለወግ ማዕረግ የሚያበቁባት ለማድረግ በትጋት ማገልገላችን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.