አዲስ አበባ “የብሪዝ ሲቲ ( Breathe Ci...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ “የብሪዝ ሲቲ ( Breathe Cities)” ከተሞችን ተቀላቀለች!

“ብሉምበርግ”  የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ የአየር ጥራትን ለማሻሻል 45 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ በዓለም ላይ ከተመረጡ ከተሞች ጋር በቀጣይ ለመስራት ባስታወቀበት ወቅት ነው።
 
አዲስ አበባ “የብሪዝ ሲቲ” ፕሮግራም ስትቀላቀል፣ በከተማዋ የአየር ጥራትን ለማሻሻል የሚደረገውን ስራ የበለጠ ይደግፋል።
 
ዛሬ በለንደን የአየር ንብረት ለውጥ ትግበራ ሳምንት ፕሮግራም ላይ በተገለፀው፣   አዲስ አበባ የብሪዝ ሲቲ ከተሞች አባል መሆን የተረጋገጠ ሲሆን፣ ፕሮግራም በብሉምበርግ ግብረ ሠና የድርጅት፣ “በክሊን ኤር ፈንድ” እና “በሲ40 ሲቲስ” አማካኝነት የሚደረግ ድጋፍ ሲሆን፣ አላማውም የከተማችንን የአየር ጥራት ለማሻሻልና ከአየር ጥራት ጋር ተያይዞ የሚመጣው የጤና ጉዳት ለመቀነስ ያለመ ነው። ይኽም አዲስ አበባን ጨምሮ በ16 ዓለማቀፍ ከተሞች የሚተገበር ይሆናል። 
 
የፕሮግራሙ መገለፅ ተከትሎ፥ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተወካያቸው “አዲስ አበባ የብሪዝ ሲቲ አባል መሆኗ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፣ በከተሞቻችን የኮሪደር ስራ እያሳየን ያለውን ሁለንተናዊ የላቀ የከተማ ትራንስፎርሜሽን፥ ፅዱ፣ ውብ፣ አረንጓዴ እና ለመኖር ምቹ ከባቢን ከመፍጠር ስራችን ጎን-ለጎን የአረንጓዴ አሻራ፣ የብስክሌት መንገድ እና የአየር ጥራት መቆጣጠርያ መሣርያዎችን የበለጠ አስፋፍተን እና አጠናክረን ለመስራት ያግዛል ብለዋል። 

ጨምረውም “በማይክል ብሉንበርግ እንዲሁም በሚመሩት የግብረሰናይ ድርጅት እየተደረገልን ያለው እገዛም ይህንን አጠናክረን ለመስራት ያስችለናል። እንዲሁም አዲስ አበባ የኮፕ 32ን ስታዘጋጀት በአየር ጥራት ቁጥጥር እና የአየር ጥራትን ማሻሻል የሚያስችሉ ተሞክሮዎችን ለሌሎችየአፍሪካ ከተሞች ብሎም ለአለም አቀፍ  ከተሞች ተሞክሮ ለማሳየት ያግዘናል” ብለዋል ።
 
የተባበሩት መንግታት በአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ እና የብሉክ ብሉምበርግ ግብረሰናይ ድርጅት ዋና መስራች ማይክል ብሉንበርግ  በበኩላቸው፣ “በብሪዝ ሲቲስ አማካኝነት የከተማ ከንቲባዎች እንዲሁም መሪዎች የአየር ጥራትን ከማሻሻል አንጻር  ግንባር ቀደም ሆነው መስራታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ገልፀዋል። 

እያንዳንዱ ከተማ ወደፊት አየር ጥራትን ከማሻሻል አንጻር የሚወስደው እርምጃ ሕይወትን ለማዳን፣ የሕዝብ ጤናን ለማሻሻል እና የብክለትን ልቀትን ለመቀነስ ይረዳል - ይህም ከተሞች ለመኖርና ለመሥራት የተሻሉ ቦታዎችን ያደርጋል። ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት ወይም ድጋፍ ከንቲባዎች እያደረጉ ባለው ስራ ተጨማሪ እገዛ ያደርጋል  - ከነዚህ ስራዎች የሚገኙ ተሞክሮዎችንም ደግሞ ወደ ተጨማሪ ከተሞች ለማዳረስ  ይረዳል”ብለዋል። 
 
አሁን ከተቀላቀሉት አዲስ አበባ እና ማድሪድ ከተሞች በተጨማሪ፥ አክራ፣ ባንኮክ፣ ቦጎታ፣ ብራስልስ፣ ጃካርታ፣ ጆሃንስበርግ፣ ለንደን፣ ሜክሲኮ ሲቲ፣ ሚላን፣ ናይሮቢ፣ ፓሪስ፣ ሪዮ ዴ ጄኔሮ፣ ሶፊያ፣ እና ዋርሶ ይገኙበታል። ይህም ብክለትን ለመቀነስ እና የህዝብ ጤናን ለማሻሻል የሚሰሩ የከንቲባዎች አውታረ መረብ ይፈጥራል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.