ዜና ሹመት ወ/ሮ ሀንጋቱ መሀመድ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተሾመዋል ።
ዜና ሹመት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በብልጽግና ፓርቲ አ/አ/ቅ ጽ/ቤት የጤናና አረንጓዴ ልዩ ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ አመራር በመሆን ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ በላቀ የአመራር ብስለት ሲመሩ የነበሩት ወ/ሮ ሀንጋቱ መሀመድ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተሾመዋል ።
ወ/ሮ ሀንጋቱ በስራ ልምዳቸው፥ ከወረዳ እስከ ዞን እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል በመሆን በአመራርነት ተመድበዉ በብቃትና በጥሩ ሥነ-ምግባር ሲያገለግሉ የቆዩ ጠንካራ መሪ ናቸው።
በተጨማሪም የጤና ቢሮ አማካሪ የነበሩት ወይዘሮ ብርቱካን አህመድ ከክልል እስከ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ባላቸው ከፍተኛ የአመራር ልምድና ብቃት የከነማ ፋርማሲን በዋና ስራ አስኪያጅነት እንዲመሩ ተሾመዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ፣ ሰራተኞች እንደሁም የቢሮው የብልፅግና ህብረት አመራሮችና አባላት ለወ/ሮ ሀንጋቱ መሀመድ እና ለወይዘሮ ብርቱካን አህመድ በተመደቡበት የስራ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡት በመተማመን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
#Ethiopia
#addisababa
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.