በ79.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው ዘመናዊው የሀማሳ ሞዴል መንደር ዛሬ በይፋ ተመርቋል።
መንደሩ የአርሶ አደሩን ኑሮና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ ዘመናዊ የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የእንስሳት ማደሪያ፣ የአትክልት ስፍራ፣ የባዮ ጋዝ እና የንብ ቀፎዎች የተሟሉለት በመሆኑ ለነዋሪዎች ሁለንተናዊ ብልጽግናን ያረጋግጣል።
ይህ ሞዴል መንደር የገጠሩን ማህበረሰብ ክብር፣ ምቾት እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ የሪፎርማችን ህያው ፍሬ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.