የአዲስ አበባ ወንዞች የውበት እና የጤና ምንጭ መሆን ችለዋል!
ከቅርብ አመታት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ከተማዋን የማይመጥኑ የቆሻሻ መጣያና ማከማቻ የነበሩና በአጠገባቸው ለማለፍ አፍንጫ የሚሰነፍጡና ብዙዎችን ለተለያዩ የጤና እክል የዳረጉ ነበሩ፡፡ ዛሬ ላይ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል፡፡ ከተማዋ ወንዞች አክማ ትላንት ከተዘፈቁበት አስከፊ ገጽታ አላቃ የውበት እና የጤና ምንጭ እንዲሆኑ እያደረገች ትገኛለች፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ትኩረት የሚገነቡት እነዚህ የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክቶች ማራኪ ስፍራዎችን ያካተቱ የተፈጥሮ ሚዛን የጠበቁ፣ አረንጓዴ ስፍራዎችና ውብ የእግር መጓዣ መንገዶችን ያሟሉ ለወጣቶችና ለህፃናት መጫወቻ ሜዳዎችን ያሟሉ ማህበራሰቡ በእግር የሚጓዝባቸው እና ጤናውን የሚጠብቅባቸው ብሎም የጋራ ጊዜ የሚያሳልፍባቸው አዲስ መልክና ዘመናዊ ገፅታን የተላበሱ የከተማዋ የውበትና የደስታ ምንጭ ናቸው፡፡
ለአብነትም በቅርቡ ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት የሆነው እና ከእንጦጦ አንስቶ ቀበና የሚዘልቀው የወንዝ ዳርቻና ቀበና ድልድይ በውስጡ አስገራሚና አስደናቂ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ ለነዋሪዎች አዲስ የምስራች ይዞ ብቅ ብሏል።ይህ ፕሮጀክት የወንዞችን ህልውና ከመታደግ ባለፈ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት አኗኗርና እንቅስቃሴ ያሻሻለ እንዲሁም የከተማዋን የቱሪስት መስህብ በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ተደማሪ ስኬት መሆን የቻለ ነው፡፡
ለሀገር አሳቢ በሆኑ ቅን ልቦች የተገነቡት እነዚህ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች የማህበረሰቡ ችግር መሆናቸው አብቅቶ ዛሬ ላይ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ለከተማው አዲስ ውበት እና ተጨማሪ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.