ኢትዮጵያ ማከናወኗን ቀጥላለች!
ዛሬ ያስመረቅነው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብራችን ያፈራው ሌላኛው ታላቅ ስኬት ነው። ይህ ዘመናዊ ሪዞርት ከ1,300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን ያካተተ ሲሆን፤ ከመዲናችን ባሻገር የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕያችንን ያጠናክራል፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብም ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ዳያስፖራውና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን አዲስ የሀገራችንን ዕንቁ ስፍራ በመጎብኘትና በመጠቀም፣ የኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ምዕራፍ በጋራ እንድንቋደስ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
ETHIOPIA KEEPS DELIVERING!
Today, we inaugurated the Arba Minch Conference Resort, another magnificent outcome of our 'Dine for Generation' initiative. This modern resort features state-of-the-art infrastructure, including a conference hall capable of hosting over 1,300 people and a unique floating restaurant on the lake. It will strengthen our vision of making Ethiopia a hub for international forums by expanding conference tourism beyond our capital city, while creating vast employment opportunities for local residents.
I call upon all our citizens, the diaspora, and the international community to visit and experience this new jewel of our nation, and to take part in this new chapter of Ethiopia's tourism and conference sector!
#EthiopiaDelivers #MeetInEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.