አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በቴክኖሎጂና በአሰራር የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በቴክኖሎጂና በአሰራር የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በቴክኖሎጂና በአሰራር የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡ 

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ“አሸናፊ ትውልድ” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርኃ ግብሩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ በአዲስ አሰራር በአዲስ ቴክኖሎጂ በዘመነ የሚዲያ መሰረተ ልማት ሚዲያውን በፊት አውራሪነት እየመራ ይገኛል ብለዋል፡፡ 

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመናዊ የሆነ ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ የአሰራር ስርዓቶችን በማዘመን ብርቱና ንቁ የሆኑ ጋዜጠኞችን እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎችን በማሰማራት በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ስራዎች ወደ ህዝብ እንዲደርሱ እያደረገ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

የዛሬው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መርሃ ግብር ሚዲያውን የበለጠ ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ በመግለጽ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በቴክኖሎጂና በአሰራር የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሞገስ ባልቻ ገልጸዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.