ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል።ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከመመገብ ባሻገር!!

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከመመገብ ባሻገር ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት እና ለነዋሪዎቻችን  ፍቅርና ክብር ከሰጠንበት ስራዎች አንዱ  የሆነውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል።
 
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 4ኛ ቅርንጫፍ የሆነው ይህ 30ኛው የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከቂርቆስ፣ ከሸራተን ማስፋፊያ እና ከካሳንቺስ አካባቢ  ህጋዊ ቤት ሳይኖራቸው በጥገኝነትና በደባልነት ይኖሩ የነበሩ አቅመ ደካሞች ፣ ምንም ቋሚ ገቢ ያልነበራቸው ፣ አራብሳ  ቤት ሰርተን ያስገባናቸው አረጋዊያን እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ነዋሪዎቻችን የሚኖሩበት  አካባቢ በመሆኑ የምገባ ማዕከል በመጀመር ጊዜያዊ ችግራቸውን በማቃለልና  በዘላቂነት ቋሚ የሥራ እድል እንዲያገኙ የሚያስችል ስራም የጀመርንበት ማዕከል ነው።

በከተማችን የገነባናቸው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት  ሰው ተኮርነታችን በተግባር የሚገለጥባቸው፣ ጊዜያዊ ችግሮችን የምንፈታባቸው ሲሆኑ በዘላቂነት ደግሞ ሌት ተቀን በመስራት  ሃገራችንን ለማበልፀግ ግባችንን ለማሳካት እንተጋለን።
 
 በከተማችን ማህበራዊ ሃላፊነትን  መወጣት እያደገ የመጣ ሲሆን፤ ዛሬም ካላችሁ  በማካፈል  አብራችሁን የሰራችሁ እንዲሁም በማዕከሉ በቋሚነት ለመመገብ ቃል የገባችሁ  በጎ አድራጊዎችን በተጠቃሚ ነዋሪዎቻችን ፣በከተማ አስተዳደራችንና በራሴ ስም አመሰግናለሁ።
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.