‎#የጠሚሩምላሾች

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

‎#የጠሚሩምላሾች

የትግራይን አሁናዊ ሁኔታ በሚመለከት፦

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በርካታ ጥቅሞችን ያስገኘ ቢሆንም፣ ለምን ተስማማችሁ በሚል ያኮረፉ በርካታ ኃይሎች ተፈጥረዋል። ከሕወሓት ባሻገር፤ በትግራይ ላይ ጥፋት ሊቀጥል ይገባ ነበር ብለው የሚያስቡ አካላት በማኩረፍ ከእኛ የራቁ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ እርስ በእርስ ለመተባበር የሞከሩበት ሁኔታ አለ።

አሁን ላይ በትግራይ ባሉ ኃይሎች በየቀኑ አዳዲስ ግጭቶችንና ጦርነትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች እየተፈጸሙ ይገኛሉ። ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነውና የከፋው ጉዳይ ግን በአሁኑ ወቅት በርካታ የትግራይ ወጣቶች በጉልበት ታፍሰው በሱዳን እየተካሄደ ላለው ጦርነት እንዲሰለፉ መደረጉ ነው። እነዚህ ወጣቶች በማያውቁትና በማይመለከታቸው ጉዳይ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ሕይወታቸውን እያጡ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሳይበቃ፣ ጉዳዩ ወደ ሱዳንም ተሻግሯል።

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ የትግራይ ሕዝብ የችግሩ ፈጣሪ ሳይሆን፣ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው። የትግራይን ሕዝብ ይበልጥ የጎዳውና ጉዳቱን ያባባሰው የማይታይ የውስጥ ቁስል መኖሩ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ የውስጥ ቁስል ደግሞ በቀላሉ የማይሽር ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ዛሬ በትግራይ ውስጥ ከሚኖረው ይልቅ በደሴ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ እና በአዳማ በሰላም እየኖረና ያለምንም ስጋት ወጥቶ የሚገባው የትግራይ ተወላጅ ቁጥር ይበልጣል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በተመለከተ፦

‎ጠላቶቻችን ‘3መ’ን መርህ አድርገው ይከተላሉ፤ አንደኛው ‘መ’ መካድ ነው፤ ኢትዮጵያ ድልብ ሀብት ያላት መሆኗን፣ አልገዛም ያለ ህዝብ ያላት መሆኗን፣ ኢትዮጵያን ማንበረከክ ቀላል አለመሆኑን ቢያውቁም ግን ይክዳሉ። ሁለተኛው ‘መ’ መርሳት ነው፤ ስልታዊ ጥልቀት ያላት ሀገር መሆኗን፣ የወጣት ሀገር መሆኗንና ከከፋም እራሱንና ሀገሩን መከላከል እንደሚችል እንዲሁም የሀገሪቷ አቀማመጥም ሆነ ተቋማዊ ልምምድ ቀላል አለመሆኑን መርሳት፤ ስለእኛ ሲያስቡ እምቢ ባይነታችንን ይዘነጋሉ። ሶስተኛው ምኞት ነው፤ ያለፈበት ስልት እስረኛ የመሆን ምኞት፤ ሀገር ውስጥ ያሉ ጽንፈኞች ከውጪ ጠላቶች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን አሸንፋለው ብሎ መመኘት። እውነታው ግን ማንም ቢመጣ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ቅንጣት ታክል ስጋት የለብንም፤ ያንንም ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም እየገነባን ነው!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.