ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውን የአባይ ድልድይ መርቀዋል።
ይህ ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ ነው። የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የአባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ ይሆናል።
#PMOEthiopia
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.