የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በጉ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረውና ለ30 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የአውሮፕላን ማረፊያ፤ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎና ደረጃው ከፍ ብሎ ተገንብቶ ዛሬ በይፋ አስመርቀናል።

በ2,400 ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ላይ የተገነባው እንደ Q400 እና B737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚያስችል ከፍተኛ ዐቅምም ፈጥሯል። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ መጀመሩ የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለአካባቢው እና ለመላው ሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል።

ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስና የጀመርናቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለምርቃት ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየን እንቀጥላለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.