የኮሙኒኬሽን ስራችን በተመለከተ:-
መረጃዎች ለሕዝብ የማድረስና ግልፅነት የመገንባት ስራዎች በሚመለከት በእነዚህ የለውጥ አመታት የከተማው ኮሙኒኬሽንና ሚዲያዎች የመንግስትን ድምፅ የሚያስተጋቡ ብቻ ሳይሆኑ የሕዝቡን ልሳን እንዲሆኑ ጭምር ስትራቴጂ ተቀርፆ ተሰርቷል፡፡ በዚህም ስትራቴጂክ የዘመን ምዕራፍ ውስጥ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማትና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር የተቀናጀና የተናበበ አሠራር በመዘርጋት፣ የከተማዋንና አገራዊ አጀንዳዎችን ማዕከል ያደረጉ መረጃዎችን በተለያዩ የተግባቦት አማራጮች ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ፣ በመንግስት አሠራሮች ላይ ግልጸኝነትን የመፍጠርና ግንዛቤን የማሳደግ ሰፊ ተግባራት ተከናውነዋል።
እነዚህ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የተቀናጁ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች በመንግስትና በሕዝብ መካከል የጋራ መግባባትና ጠንካራ መተማመን እንዲፈጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፣ የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማጎልበት ባለፈ የከተማዋን መልካም ገጽታ በላቀ ደረጃ ለመገንባትና ለማስተዋወቅ አስችለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.