ስለ ህጻናት ሁለንተናዊ አስተዳደግ ለወላጆች እና አሳዳጊዎች የምክር አገልግሎት የሚሰጡ 3085 ባለሞያዎችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ልምድ ለመቅሰም ወደ ከተማችን የመጡ መሪዎች በተገኙበት አስመርቀናል።
ባለፈው ዓመት በመጀመሪያ ዙር 2200 ባለሞያዎችን አሰልጥነን በማስመረቅ ወደ ስራ ያሰማራን ሲሆን አሁን ከተመረቁት ጋር በአጠቃላይ ከ 5200 በላይ ለወላጆች የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ባለሞያዎችን አሰልጥነን ወደ ስራ አስገብተናል።
አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ የማድረግ ስራችን በተጨባጭ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.