የከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎ
የከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በከተማችን ተቋማት ላይ ያዘጋጀው የሥራ አፈጻጸም እና የኦዲት ሪፖርት ላይ ለምክርቤት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት በሙሉ ድምፅ
የኦዲት ሪፓርቱ የሸፈነዉ 107 የመንግስት ተቋማትን ሲሆን የኦዲት አገልግሎት አይነቱ የፋይናንስ እና ህጋዊነት ኦዲት፥ ክዋኔ ኦዲት፥ የገቢ ኦዲት፥ የአካባቢ ኦዲትና የማጭበርበር ወይም ልዩ ኦዲት ናቸዉ።
የኦዲት ሥራዉ ዓለም አቀፍ የኦዲት ደረጃዎችን እና የኢትዮጵያ መንግሥት የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን ተከትሎ እያከናወነ ነው ።
በዚሁ አግባብ ግኝቶቹ:-
ከንቲባ ጽ/ቤትን፥ ሥራና ክህሎት ቢሮንና ፕላንና ልማት ቢሮ ጨምሮ በ26 ተቋማት በተደረገው ኦዲት የተቀመጡትን የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎችና አሰራሮችን ጠብቆ ምንም ነቀፌታ ያልተገኘባቸው፥ 49 ተቋማት ጉልህ ነቀፈታ ያልተገኘባቸው በመሆኑ በአጠቃላይ ኦዲት ከተደረጉት 70% ሲሆኑ ፤ 31 ተቋማት በተለይም የወረዳ ፅ/ቤቶችና ኮሌጆች የሂሳብ አያያዛቸዉ ችግር ያለበት መሆኑን የኦዲት ሪፖርት ግኝቱ ያሳያል።
በከተማችን የህዝብን ሃብት እና ንብረት እንዳይባክን፥ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የኦዲት መስሪያ ቤቱ የክትትል ስራዎች በጥንካሬ የሚወሰድ ነው።
በኦዲት ግኝት መሰረት መታረም የሚገባቸው እያረሙ፤ የአቅም ችግር ያለባቸው የፉይናስ ሰራተኞችን በአቅም ግንባታ እንዲደገፉ ማድረግና የኦዲት ማጠናከር እንዲሁም ተቋማት ላይ ቀጣይ ክትትልና እርምት እየተወሰደባቸው የሚኬድ ይሆናል።
ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት በአጠቃላይ የከተማዋ ገቢና ወጪ ጤናማ መሆኑን አረጋግጧል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.