የአዲስ አበባ ከተማ የ2019 በጀት ዓመት 502...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ የ2019 በጀት ዓመት 502 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ!

ምክር ቤቱ ባካሄደዉ 3ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ በሁለተኛ ቀን ውሎው የአዲስ አበባ ከተማ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ የተወያየ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ በጀት 502 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር እንዲሆን  በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የፀደቀው በጀት ከባለፈው የ2018 ዓ/ም ተመሳሳይ በጀት ጋር ሲነጻፀር የ152 ነጥብ  26 ቢሊዮን ብር  ወይም 43 ነጥብ 5  በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጻል፡፡

ከፀደቀው በጀት ውስጥ  359 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለካፒታል፣ 142 ነጥብ 97 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ እንዲሁም 16 ቢሊየን ብር  የመጠባበቂያ በጀት መሆኑ ተገልፀዋል። 

በጀቱ፥ የከተማ አስተዳደሩን የ10 እና የ5 ዓመት የልማት ስትራቴጂዎች ግቦችንና እና የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማሳካት ያለመ ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ማረጋጋትና የኑሮ ዉድነትን ለማቃለል፣ የስራ እድል፣  ፈጠራ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር፣ የመሠረተ-ልማት ግንባታና ጥገና በዘላቂነት ማረጋገጥ፣ የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ኮሪደር ልማትን ጨምሮ መጠበቅና ለማስቀጠል የሚውል ነው። 

እንዱሁም የትራንስፖርትና የትራፊክ ፍሰትን ማሻሻል፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ብልሹ አሰራርንና ሌብነትን ማስቀረት፣ የሰዉ ሃብት ልማት የማስፈፀም አቅምን መገንባት፣ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ፣ የቤት ልማት ማጠናከር የዉሃ አቅርቦት እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በተሟላ ለማጠናቀቅ እና የመንገድ መሰረተ ልማት ለማስፋፋት የሚዉል መሆኑ በቀረበዉ የበጀት ማብራርያ ተመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.