የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የሚድያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የሚድያ ቤተሰብ "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ!

 


በቢሮው አስተባባሪነት እና አሰባሳቢነት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አመራሮች፣ የመንግስት እና የግል ሚድያ አመራሮች፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅር የኪነጥበቡ ቤተሰብ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰብ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበረሰብ አንቂዎች በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ አካሔዱ። 

በመርሐ-ግብሩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሄር በአስተላለፉት መልዕክት፣ “የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተቋማት  እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ ባሉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች የጀርባ አጥንት በመሆን በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ ከማገልገል በተጨማሪ፣ አሰባሳቢ የወል ትርክትን በማስረፅ፣ የሀገር አንድነት እና ሉአላዊነትን የጠራ ዕሳቤ ያለው ትውልድ ከመፍጠር አንፃር ትርጉም ያለው ስራ እየሰራ ይገኛል። 

እንዲሁም፥ የአረንጓዴ አሻራችን ሽፋን እና ስፋት ተከታታይ ዘገባዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችንና የዜና ሽፋኖችን በግንባር ቀደምነት የመረጃ ምንጭ ሆኖ በመስራት፣ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ፣ ጠንካራ ተግባቦት ከመፍጠር አንፃር ውጤታማ ስራ እየሰራ ይገኛል። 

ዛሬም የሚድያ ቤተሰብ ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ቁልፍ ተግባራቱ በተጨማሪ፣  “ተስፋን እንትከል“ በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር 8 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አንዱ አካል በመሆን የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመፍጠር  በየካ ክፍለ ከተማ ቀበና የወንዝ ዳርቻ ተገኝተዉ ችግኝ በመትከል ታሪካዊ አሻራቸዉን ማኖራቸዉ፣ በአረንጓዴ አሻራ በዓለም መድረክ ያገኘነዉን እዉቅና ከማጠናከር ባሻገር  ድርብ ኃላፊነታቸዉን መወጣት መቻላቸዉን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉ የቢሮዉ ኃላፊ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የሚድያው ቤተሰብ በከተማዋ ሁለንተናዊ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆነው በትዉልድ እና በሃገር ግንባታ ላይ ሙያዊ ግዴታቸዉን ለመወጣት ድርብ ኃላፊነት ያለባቸዉ መሆኑንና ይህንንም ወደ ተግባር ለዉጦ የተፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት የጀመሩትን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.