ዛሬ ከከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በኤአይ( AI) ዩኒቨርሲቲ አካሂደናል።
“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን እንገኛለን።
የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሰኔ 7/2018 ዓ.ም አስጀምረን እስከአሁን 4,469,710 ችግኞችን የተከልን ሲሆን፣ አፈፃፀማችንም 75 በመቶ ደርሷል። ችግኝ መትከል ብቻውን ከምናልመው ግብ ስለማያደርሰን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራም እንሰራለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.