የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ ታሪካዊ በሆነው የሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በታሪክ ምዕራፍ ላይ ታላቅ ስፍራን የሚይዝ ነው ብለዋል።

ይህ አይነቱ ሀገራዊ ምክክር የሀገራችንን ማህበራዊና የፖለቲካ ጉዞ የሚያቀና እንዲሁም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የሀሳብ ልዩነቶች ውበት ቢሆኑም፤ ነገር ግን እነዚህን ልዩነቶች በሀይልና በግጭት ለመፍታት የተሄደበት ሁኔታ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንደማይችል የኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ ምስክር ነው።

‎በመሆኑም ለዘላቂ መፍትሔ እንዲሁም የወደፊት እጣ ፈንታችን ላይ በጋራ እንድንስማማ የሚያስችለንና ለሀገራችን ፈውስ የሚሆነው ብቸኛ መድኃኒት ታማኝ፣ ግልጽና አካታች ሀገራዊ ምክክር መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.