ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia (የኸርት አታክ ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑን በጽ/ቤታችን ተቀብለናቸዋል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለ5ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia (የኸርት አታክ ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑን በጽ/ቤታችን ተቀብለናቸዋል።
የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ በፍቅር የምትሰጡት እጅግ የላቀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከልብ የሚደነቅ ነው ።
በቀጣይም የህክምና ተራ እየጠበቁ ላሉ የልብ ህሙማን ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ በጋራ ተቀናጅተን የብዙዎችን ሕይወት ለመታደግ አብረን ለመስራት ተስማምተናል።
እንደዚህ ትልቅ የህክምና ቡድን አቀናጅታችሁ ለወገኖቻችሁ ትልቅ ህይወትን የማዳን ስራ ለመተግበር የተጋችሁ መስራቾቹን እና የበጎ ፍቃድ የህክምና ቡድኑን አባላት በራሴ እና በታካሚዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.