በምናብ ያየነውን አቅደን ተግተን ፈፅመናል፤ 96...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በምናብ ያየነውን አቅደን ተግተን ፈፅመናል፤ 96 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ስናካሄድ የነበረው  የ2018 በጀት ዓመት እና የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዳ አፈፃፀም ግምገማ በስኬት አጠናቅቀናል። 

በግምገማችንም  ያቀድናቸውን ስትራቴጂክ ግቦች በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር   24/7 በተለወጠ የስራ ባህል በትጋት ሰርተን  የተመዘገቡ   ውጤቶችን ማላቅ እና  የተለዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተግባብተናል።

 ባለፉት አምስት ዓመታት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የአገልግሎት አሰጣጣችን ዲጅታላይዝ በማድረግ በተለይም ደግሞ  በያዝነው በጀት ዓመት ተግባራዊ ያደረግነው በመሶብ ዲጅታል  የአንድ ማዕከል የመንግስት እገልግሎት ትራንስፎርም አድርገናል፥  ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ ማንንም ያልዘነጋ ህፃናት ፥ ተማሪዎች ፥ ሴቶች፥ ወጣቶች ፥ አረጋውያን ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ልማቶች  ተግተን ሰርተናል።  2.2 ሚሊዮን የስራ ዕድል የፈጠርንበት፥ የልማታችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የገቢ አሰባሰብ ስርዓታችን እጅግ ውጤታማ የነበረበት፥  ከ60 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት የፈፀምንበት፤  ከተማችን  ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ፤  አዲስ አበባ ስሟና ግብሯ የተናበበ ፅዱ ፥ አረንጓዴና ውብ ከተማ የማድረግ፤  በአፍሪካ ብቻም ሳይሆን በዓለም መድረክ ጎልታ እንድትታይ አልቀን ፈፅመናል።  

 ከስኬቶቻችን ባሻገር ዛሬም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች የአመራራችን የውጤታማነት ልዩነቶች፣ የስነምግባር መጓደል፣ የመረጃ አያያዝ ክፍተቶችን ለማረም እንሰራለን እንዲሁም በቀጣይ  የኑሮ ውድነት እና የገበያ ማዛባትን ማስተካከል፥ የስራ እድልን ማስፋት፥ ፅዳትን ባህል ማድረግ፥ አገልግሎትን ማዘመን ፣ የመሶብ ዲጅታል አንድ ማዕከልን ማጠናከር፣ የቤት፥ ትራንስፖርት፥  መንገድ፥ ውሃ አቅርቦት ማሻሻል፥ የከተማ ማደስ  በአጠቃላይ የጀመርነውን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን የምንሰራ  ሲሆን ጠንካራ መንግስት የመመስረት ስራም
ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ እና የመረጠንን ህዝብ ይበልጥ በቅንነት ፣ በታማኝነትና በትጋት የምናገለግል  መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.