በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ የልማት ስራዎች መዲናዋን የዓለም አቀፍ ትኩረት ማዕከል አድርገዋታል!
አዲስ አበባ ልክ እንደ ስሟ አዲስ እና ማራኪ ሆና በድጋሚ እየተወለደች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ የኮሪደር፣ መልሶ ማልማት እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ እየቀየሩት ነው።
ከጫፍ እስከ ጫፍ የተዘረጉ ዘመናዊ መንገዶች፣ ለእግረኞች እና ለብስክሌተኞች የተሰናዱ ምቹና ደህንነታቸው የተጠበቁ መንገዶች፣ እንዲሁም ለዓይን ማራኪ አረንጓዴ ስፍራዎችና መናፈሻዎች ከተማዋን ለነዋሪዎቿ እጅግ ምቹ እና ስሉጥ የኑሮ ከባቢ እንዲኖራት አድርገውታል።
የዚህ ታላቅ ለውጥ ሌላው አስደናቂ ገጽታ ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነት መረጋገጡ መሆኑ ሲሆን፣ በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይወሰን በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ሰፈሮች ውስጥ በእኩል ደረጃ እየተዳረሰ ይገኛል።
ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በድምቀት አስጠብቃ፣ ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎችን የሚያሟሉ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት የኮንፈረንስ ቱሪዝም ዋና መዲና መሆን ችላለች።
ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመጡ ታላላቅ እንግዶች የሚጎርፉባት፣ በንግድ፣ በባህልና በዕውቀት ልውውጥ ደምቃ የምትታይ፣ ቀንና ሌሊት እግር የሚበዛባት ሕያው ከተማ ሆና የምትቀጥለው መዲናችንን በሁሉ አቅጣጫ አብባና አምራ ማየት የጋራ ኩራት ነው።
ይህቺን ታላቅ መዲና በጋራ ጠብቆና ከፍ አድርጎ ማስቀጠል ደግሞ የሁላችንም ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.