ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ታላቁን የዓባይ ወንዝ ድልድይ ለማስመረቅ በባሕር ዳር ከተማ የተገኙ ከፍተኛ አመራሮች በ"ጽዱ ኢትዮጵያ "ቴሌቶን ላይ በጋራ ተሳትፈዋል::
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ከፍተኛ አመራሮች የሚችሉትን ሁሉ ሲያበረክቱ መቆየታቸውን ገልጸው÷ ዛሬም በአንድነት በመሆን ለዚሁ ተብሎ ወደ ተዘጋጀው የሒሳብ ቁጥር ገቢ እንዳደረጉ ተናግረዋል።
በጽዱ ኢትዮጵያ ቴሌቶን በአንድነት ሆነው ገቢ ካደረጉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙበት አሚኮ ዘግቧል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.