አዲስ አበባ፣ የመንግስትን አገልግሎት የሚያዛባ ስትቀጣ፤ ህዝብን በማገልገለል በተከታታይ የላቀ ውጤት ለሚያስበዘግቡ ተቋማትም የምትሸልም፣ የምታበረታታ ከተማ ናት!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ብክነትን በመቀነስ፣ የመንግስትና የህዝብን ሀብት ከሌብነት እና ብልሹ አሰራር በመጠበቅ የልማት ስራዎችን በማጠናከር ጉልህ ስራ ሰርተዋል፡፡ ይኸውም፣ ለዘላቂ ልማት እና ድህነት ቅነሳ የሚውለው ወጪ ድርሻ ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት 47 በመቶ በማስተካከል፤ 72 በመቶ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ጠቀሜታውም በተግባር መሬት ላይ ታይቷል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ60 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶችን በጥራት ማጠናቀቅ አስችሏል፣ ዓለምን ድንቅ ላሰኘ፣ ኗሪዎቿን ያስፈነደቀ-በሀሴት ለሞላ ሁሉን-አቀፍ መሠረተ-ልማት ውሏል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል፡፡
ያምኾኖ፥ በዚህ ሁሉን-አቀፍ የልማት ርብርብ መሀል፣ በበልሹ አሰራር እና ሌብነት የተገኘን፣ በመልካም አስተዳደር ጉድለት እና የመንግስትን አገልግሎት የሚያዛቡ አመራሮችም ሆኑ ባለሙያዎች፣ ከጅምሩ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን “ቀይ መስመር” ነው ብሎ የተነሳው አስተዳደሩ፥ 2, 560 ለሚሆኑ ተግሳፅ፣ የፅሑፍ ማስጠንቀቅያ፣ ከሃለፊነት ዝቅ የማድረግ እና በህግ ተጠያቂነት እያደረገ፣ እየቀጣ ያለ ከተማ ነው፡፡
በሌላ መልኩ፥ ብልሹ አሰራርን እና ሌብነትን በመፀየፍ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ የመንግስትን አገልግሎት እንዲቃና እና እንዲዘምን የበለጠ ህዝባቸውን በማገልገል ሌት-ተቀን በመስራት በተከታታይ የላቀ ውጤት ላመጡ የተቋማት ስራተኞች እና አመራሮችም ሽልማትና ማበረታቻ የምታበረክት ከተማም ናት፡፡
ይኽም የከተማዋ ተጨባጭ የዕድገት ጉዞ ይበልጥ ለማጠናከር፣ በተቋማት መካከል አዎንታዊ የፉክክር መንፈስ በማሳደር የአገልግሎት አሰጠጥ እና መልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በዘላቂነት ማስቀረት እንዲቻል፣ የስራ ተነሳሽነት እንዲጎለብት ዕድል ይሰጣል፤ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.