ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የእንጦጦ - ቀበናን የወንዝ እና የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ጎበኙ
የብልፅግና ፓርቲ ዋናው ማዕከል እና የክልል ቅ/ፅ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በመዲናዋ በመፍጠር እና በመፍጠን የተገነቡ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክቶችን ተዟዙረዉ ጎብኝተዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋናው ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና ሌሎችም የፌዴራል ፣ የአዲስ አበባ እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የብልፅግና ፓርቲ ምናብ ወደ ውጤት እየተቀየረባት የምትገኘው ውቧ መዲናችን ሁሌም አዲስ እየሆነች እንደምትገኝ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ የብልፅግና አይቀሬነት ማሳያ መሆኗን የገለፁት ከንቲባ ተግተን በመስራት በላቁ አዳዲስ ድሎች እንገናኛለን ብለዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች የከተማችንን ገፅታ ከመገንባታቸው ባሻገር የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ከፍ ማድረጋቸውን አስረድተዋል።
ከፍተኛ አመራሮች 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የህፃናት መጫዎቻዎች፣ የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ ሱቆች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ቤተ መፅሀፍት ፣ የከተማችን ነዋሪ አንዱ የመዝናኛ ማዕከል የሆነውን የቀበና ግድብ እና ሌሎችም የህዝብ መገልገያዎች ያሉትን የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ ዳር ፕሮጀክትን ተዟዙረዉ ጎብኝተዋል፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.