‎ልጆቿን የምትንከባከብ ከተማ፦ አዲስ አበባ ‎

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

‎ልጆቿን የምትንከባከብ ከተማ፦ አዲስ አበባ ‎

‎የአንድ ከተማ እውነተኛ ውበት የሚለካው በህንፃዎቿ ቁመት ወይም በመንገዶቿ ስፋት ብቻ አይደለም።

‎ትልቁ መለኪያው፣ ለነገ ትውልድ ምን ያህል ተጨንቃ እንደምትሰራ ነው።

‎አዲስ አበባ ዛሬ የምትከተለው የለውጥ ጎዳና ይህንን እውነታ በተግባር የሚያሳይ ነው።

‎የከተማዋ ገጽታ ግንባታ ስራዎች፣ ከወንዞች ልማት እስከ አረንጓዴ ስፍራዎች መስፋፋት ድረስ፣ ለነዋሪው ምቾት ብቻ ሳይሆን ለልጆችም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የሚያምር አካባቢ ለመፍጠር ታስበው የተከናወኑ ናቸው።

‎እንደ አራዳ ፓርክ : ቀበና ወንዝ :አድዋ ድል መታሰቢያ :እንጦጦ ፓርክ፣ የወዳጅነት መናፈሻ እና አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ህጻናት በጨዋታና በእውቀት ታንጸው የሚያድጉባቸው ልዩ ማዕከላት ሆነው ተገንብተዋል።

‎ከዚህም በላይ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀጥታ የሚመሩት እና የእሳቸው ኢኒሼቲቭ የሆነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብር፣ ከልደት እስከ ስድስት ዓመት ላሉ ህጻናት ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ በመስጠት የከተማዋን የወደፊት መሠረት እያጠናከረ ይገኛል።

‎ይህ ደግሞ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርአያ ሆኖ፣ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም እንድታስተናግድ በር ከፍቶላታል።

‎ህፃናቱ ትምህርት ቤት ገብተውም ቢሆን፣ የከተማዋ እንክብካቤ አይቋረጥም።

‎ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ተማሪዎች በየቀኑ ሁለት ጊዜ ምግብ የሚያገኙበት የተማሪዎች ምገባ በአፍሪካ ደረጃ እንደ ትልቅ ተሞክሮ በዓለም የምግብ ፕሮግራም እየተጠቀሰ ይገኛል። ከምግብ ባሻገር የትምህርት ቁሳቁስና ደንብ ልብስ በነጻ በመቅረቡ፣ ልጆች ሳይራቡ፣ ሳይጨነቁ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አስችሏቸዋል።

‎ንጹህ የመጠጥ ውሃና የመጸዳጃ ቤት ተደራሽነትም በትምህርት ቤቶች እየተሻሻለ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የመማሪያ ከባቢ ለመፍጠር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበታል።

‎አዲስ አበባ ዛሬ የምትገነባው መንገድና ህንፃ ብቻ አይደለም።

‎የምትገነባው የነገዋን ትውልድ ልብ ጭምር ነው።

‎ይህች ከተማ ለልጆቿ ተስፋ፣ እንክብካቤና ምቹ አካባቢ በመፍጠር፣ ህጻናት በምቾት የሚያድጉባት የአፍሪካዊት ከተማ እየሆነች ትገኛለች።

‎ልጆቻችን ደህና ሲሆኑ ብቻ ነው፣ ነገም ደህና የሚሆነው!

‎ለተጨማሪ መረጃ፡- https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.