የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ የተቋማቱ ሀላፊዎችና አስተባባሪዎች በተገኙበት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተካሄዷል።
በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት ክላስተሩ እቅድ ይዞ ወደ ተግባር የገባዉን ያለምንም መሸራረፍ በመተግበሩ በቅንጅት በርካታ ስራዎች መስራት መቻሉን ጠቁመዉ፣ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ እንዲፈጠር ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ኩነቶች ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆኑ በመስራት የሕብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ በሆነችዉ ከተማ የጸጥታ መዋቅሩ ከላይ እስከ ታች ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ ደህንነት ላይ በስፋት ስለመሰራቱ ተናግረዋል።
ሀላፊዋ አያይዘውም በአጠቃላይ በክላስተሩ 15 ተቋማት የተሰሠሩ አበይት ተግባራትን በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን በተደራጀና በተናበበ መልኩ በመሠራቱ ዉጤታማ ስራ መሠራቱንም ጨምረዉ ገልጸዋል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የክላስተሩ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በግምገማ መድረኩ የተገኙ ግኝቶች በክላስተሩ ላይ በ2019 እቅድ ላይ በማካተት የህዝቡን ን ሁለንተናዊ ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉ እንዲሆኑ በማስቻል በቅንጅት ዉስጥ የተሠጡ ተልእኮዎችን ተቋማት እንደየ ስራ ሀላፊነታቸዉ ላቅ ባለና ተጨባጭ ዉጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዉ የፍትህ የበላይነትን በማረጋገጥ በግብ ያስቀመጥናቸዉን ህዝቡ ስጋት ዉስጥ እንዲገባ የሚያደርጉትን ስራዎች ከዚህ ቀደም ክላስተሩ እንደሰራዉ ሁሉ ከፊታችን የሚካሄዱ ትላልቅ ሁነቶች የ2019 የኢሬቻ በዓላትና የመስቀል ፣ሌሎች የአደባባይ በዓላት እንዲሁም አለም አቀፍ ሀገር አቀፍ ሁነቶች ለከተማዋ ተደማሪ የህብረብሔራዊነት መገለጫ እንዲሆኑ ክላስተሩ በበትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክላስተሩን አጠቃላይ የአመሠራረትና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በሰነድ መልክ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምጸሃይ ማሞ አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ የ15 ተቋማት ሀላፊዎች፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የፖሊስ አባላት፣የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና የማእከል ዳይሬክተሮች ሲሆኑ በመጨረሻም በክላስተሩ በ2018 በጀት አመት የእቅድ አፈጻም ተቋማቱ ለነበራቸዉ የላቀ ተሳትፎ የምስጋና የምስክር ወረቀት በማበርከት መርሃግብሩ ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.