ሃዳ አልማህዲ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሃገራዊ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሃዳ አልማህዲ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሃገራዊ ምክክር ከተፎካካሪ ፓርቲ ተወክላ የተጣለባትን ውክላና እና ሃላፊነት በታላቅ የሀገር ፍቅር እና የእኔነት ስሜት እየተወጣች እያለ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

እኛም ወ/ሮ ሃዳን በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማረፍያ ክፍል አዘጋጅተን ለአራስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አሟልተን እንኳን ደስ አለሽ ብለን ጠይቀናታል።
ወ/ሮ ሃዳ አልማህዲ  በታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ወቅት ላይ የወለደችውን ወንድ ልጅ ኮሚሽን ብላ ስም አውጥታለታለች።

 ወጣቷ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ወደ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው  እንደምትመለስ ነግራናለች። 

ህፃን ኮሚሽንም እደግ ተመንደግ! 

ለሃገራዊ ምክክር ጉባኤ በተገኙበት  የወለዱት ሁለቱም አራስ እናቶች የመጡበትን ሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለምንም ችግር አሳክተው እንዲመለሱ ለምክክሩ በቅርበት በሚመቻቸው ቦታ ማረፍያ አዘጋጅተንላቸዋል። ሁለቱንም አራስ እናቶች  ጉባኤውን አጠናቀው ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ  የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እናደርግላቸዋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.