በሁሉም መስክ ውጤታማ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን አረጋግጠናል።
ዛሬ ማምሻዉን ከመላ አመራራችን ጋር በክረምት ወቅት የምንስራቸው የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፥ የቤት ግንባታ፣የጎርፍ አደጋን መከላከል ፥ የፅዳት ስራዎች፥ የአረጓዴ አሻራ፥ ማዕድ ማጋራት፥ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ፥ ደም ልገሳ፥ ተረጅነትና ድህነት ቅነሳ ወዘተ ስራዎች አፈፃፀምን ገምግመናል።
በሁሉም መስክ ውጤታማ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን አረጋግጠናል።ሆኖም በክፍለ ከተሞች እና በተቋማት መካከል የአፈፃፀም ልዩነቶች ይታያሉ።
በቀጣይም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት መመራት የሚገባቸው፡-
👉የጀመርናቸዉን የቤቶች ግንባታን ማፉጠን፣
👉ዲቾችን ማፅዳት እንዲሁም አዳዲስ ዲቾችን መገንባት
👉ከፍተኛ ሀብት ፈሶባቸው የለሙ ቦታዎች መንከባከብ ፅዳታቸውን መጠበቅ
👉አጠቃላይ የከተማ ፅዳት ባህል እንዲሆን መስራት
👉 በግንባታ ምክንያት በተረፈ ምርቶች መንገዶችን የሚያበላሹ፥ ዲቾችን የሚዘጉ አካላት በአፋጣኝ ችግሩን እንዲያርሙ ተጠያቂም እንዲሆኑ ማድረግ
👉 በአረንጋዴ አሻራ የጀመርነው ውጤታማ ስራ ለጥራቱም ትኩረት መስጠት እንዲሁም የችግኝ ተከላ ስራ በአጠረ ጊዜ እና ከእቅድ በላይ ማሳካት
👉 የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሁሉም ዜጋ ባህል እንዲያደርገዉ የማስቻል ስራ መስራት
👉 ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በልዩ ትኩረት መስራት
👉 የጎልማሶች ትምህርት ማጠናከር
👉 ከተረጅነት ለመሸጋገር የተጀመሩ የሰብዓዊ ስራዎች ለመተግበር መጋዘኖች በጥራት የተገነቡ ቢሆንም ቀጣይ ስራ የሚሆነው በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ቁሶች እንዲኖራቸው ማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ሁሉም አመራር በጥብቅ የሚፈፅማቸው ናቸው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.