የባህልና ስፖርት ሴክተር ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የባህልና ስፖርት ሴክተር ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጎበኙ

 

ከአገር አቀፍ ደረጃ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የባህልና ስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ የስፖርትና የጥበባት ማህበራት ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እና የኪነ-ጥበብ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ መርሃ-ግብር ግንባር ቀደም ትኩረቱን ያደረገው በአዲስ አበባ የተገነቡ አዳዲስና ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ሲሆን ተሳታፊዎች በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ ሰፊ የስፖርት (መሠረተ-ልማት) ግንባታዎችን በአካል በመገኘት ተመልክተዋል።

ማዕከላቱና የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች ለወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና ለአትሌቲክስ፣ እግር ኳስ እንዲሁም ለተለያዩ የስፖርት አይነቶች ዕድገት ያላቸውን ከፍተኛ ፋይዳ ተሳታፊዎቹ በአድናቆት ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በአዲስ አበባ የተገነቡት እነዚህ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና ወቅቱ በደረሰበት ቴክኖሎጂ የተደራጁ የጥበብ ማዕከላት ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ለአገር አቀፍ የስፖርትና የኪነ-ጥበብ ዕድገት እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ብቁ ንቁ እና ውጤታማ የሆነ ወጣት   ለማፍራት እና ስፖርት ልማቱን ወደ ላቀ ደረጃ  ለማስቀጠል እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ የተገነቡት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያላቸው መሆናቸውን ገልጸው። ሌሎች ክልሎችም ከዚህ የልማት ተሞክሮ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳስበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.