በሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሁሴ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሁሴን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኘውን ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎበኙ።

የልዑካን ቡድኑ ከተማ አስተዳደሩ ሴቶችን ከአስከፊ ማህበራዊ ችግሮች አላቆ በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ለማብቃት እና እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሚያከናውነውን ሰፊ ስራ በቦታው ተዘዋውሮ በመመልከት አድናቆታቸዉን ገልፀዋል።

ጉብኝቱ በሶማሌ ክልል ተመሳሳይ ማዕከሎችን በማቋቋም ተጠቃሚዎችን ከማህበራዊ ችግር ለማላቀቅ የሚያስችል ጠንካራ ቁርጠኝነት ለመፍጠር ትልቅ ግብ ያለው  መሆኑን ተገልጿል።

የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ሁሴን በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና የልህቀት ማዕከል የሚተገብራቸው የተሳኩ የመፍትሄ እርምጃዎች እና አሰራርሮችን በመቅሰም በክልላቸው አጠናክረው ለመተግበር የልምድ ልውውጡ የጎላ ሚና ይጫወታል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.