የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በአዲስ አበባ ጉብኝት አደረጉ
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ::
የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሀፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል:: በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብትና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል::
አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.