የኮሚሽኑ ተቋማዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡ ደስታ ተስፋው(ዶ/ር)
የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በፓርቲ ዋና ጽ/ቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄዶ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ላይ በመወያየት አፅድቋል፡፡
የኮሚሸኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ደስታ ተስፋው እንደገለጹት ከማዕከል ጀምሮ እስከ ብልጽግና ህብረት ኮሚሽን ድረስ በቅንጅት በመሰራቱ እና አደረጃጀቶችን ማጠናከር በመቻሉ የኮሚሽኑ የመፈጸም አቅም ከግዜ ወደ ግዜ እያደገ እንዲመጣ አስችሏል ብለዋል፡፡
እንደዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ ወጥነት ባለው መልኩ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት በመቻሉ የተሻለ አፈጸጸም ለማስመዝገብ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
የፓርቲውን ፖለቲካዊ ጤንነት ከማስጠበቅ አኳያ አባላት በፓርቲው ውስጥ መብታቸው እንዲከበርና ሃሳባቸውነ በነጻነት እንዲያንሸራሽሩ በማድረግ እንዲሁም የፓርቲውን የአሰራር ስርዓቶችን እንዲከበሩ በማስቻል የተሻለ ውጤት እንዲመጣ አድርጓል ነው ያሉት፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር አቶ ያሲን ሀቢብ በበኩላቸው የፓርቲው ሃብትና ንብረት ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተቋማዊ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ እንዲሆንም ሚናውን ሲወጣ እንደነበር የገለጹት አቶ ያሲን አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮችን በማረም ለጠንካራ ፖርቲ ግንባታ ኮሚሽኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ እና የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እንደገለጹት ከኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶችን የተጠናከረ ክትትል ድጋፍና ግምገማ ሥርዓት ባህል እየሆነ በመምጣቱ ለፓርቲ አሰራሮች ተግባራዊነት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የኮሚሽኑን አሰራር ሥርዓት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የተቀናጀ የኮሚሽን ሥራዎች ሥርዓት እና አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት (KPI) ሥርዓት በማልማት ተግባራዊ መደረጉ ለዲጅታል ብልጽግና አካል መሆን ተችሏል ብሏል።
በመጨረሻም በኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት የለማው የተቀናጀ የኮሚሽን ሥራዎች ዲጅታል ሥርዓት(ICODiS) በባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎ በይፋ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.