በ2011 ዓ.ም በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማምረት አቅማችን አሁን ላይ ወደ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ ችለናል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ያሳደግን ሲሆን፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ የማምረት አቅማችን አሁን ላይ ወደ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ ችለናል፡፡
በተለይ ዛሬ የመረቅናቸዉ ደግሞ የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር አለም የደረሰበትን እጅግ የረቀቁ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዘላቂነት ፈርቀዳጅ ሚና አላቸዉ።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ አዲስ ፥ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ በማድረግ እና አገልግሎትን የሚያሳልጡ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ከዛሬ አልፎ ለትውልድ የምታሸጋግር ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.