በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡
***
ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አካባቢ ጓደኛቸውን ሲደበድቧት የሚያሳይ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች  በህግ እንዲጠየቁ ህብረተሰቡ አስተያየት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 መፈፀሙን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከመሰራጨቱ ከወራት በፊት ወንጀሉን የፈፀሙትን ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማጣራቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡  
በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሦስት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን  አጠናቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡  

ልጅቷ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዩ መለቀቁ በልጅቷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ  አሉታዊ  ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ቪዲዮውን የለቀቀውን አካል ለማረጋገጥ ፖሊስ ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በድጋሚ  በቁጥጥር ስር አውሎ ተጨማሪ  ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡ 
ህብረተሰቡ ድርጊቱን በማውገዝ ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳየውን  መቆርቆር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አድንቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.