ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

 

 እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም  ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ  የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ ዛሬ ያስመረቅነው የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታልም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ።
 
ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው  PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው።  በጤናው ዘርፍ የምናደርገው  ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራአስኪያጅ  ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው  አቡበከር መሃመድ ሳላህን  በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን።
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.