ዛሬ የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች እና የቦርድ ሃላፊ ክቡር ክሪስ ሆን እና ቡድናቸውን ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን አስጎብኝተናል።
ለነገዋ ጅማሮው በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ ሴቶች እህቶቻችን ተስፋና እድላቸው እዲለመልም፣ ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ከልብ በመነጨ ስሜት የተፀነሰ፣ ተፀንሶም ወደ ተግባር የተቀየረ ትልቅ ራዕይን የሰነቀ ስራ ነው።
የእነዚህ እህቶቻችንን ህይወት ለመቀየር፣ ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2016 ዓ.ም ጀምረነው በ5 ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 3,259 ሰልጣኞችን በክህሎት እና በስብዕና ግንባታ አሰልጥነን ወደ ስራ አሰማርተናል።
ዛሬ ሁሉም ተመራቂዎች ክብር ያለው ኑሮ፣ ብሩህ ተስፋን ሰንቀው አዲስ ህይወት መኖር ጀምረዋል።
“ከምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ትልቁ ስራ በሰው ላይ የምንሰራው፣ በተለይም በሴቶች ላይ የምንሰራው ነው” የሚለውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት የስራችን ማዕከል አድርገን እየፈፀምን እንገኛለን።
በከተማችን ላይ ከሚታየው ለውጥ ሁሉ የሚልቀው በለነገዋ ሴቶች ላይ እያየን ያለው ለውጥ ነው።
ለ”ለነገዋ የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል” የሰነቅነው ራዕይ፣ በዓመት እስከ 10 ሺህ ሴቶችን የሚያበቃ፣ እንዲሁም አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ልምድ የሚቀሰምበት የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ማስቻል ነው ።
ይህ ራዕይ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ሊደግፋን የመጡት የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች ክቡር ክሪስን በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አስጎብኝተን በቀጣይም በጋራ በምንሰራቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይተናል።
ለራዕያችን ግብ ስኬት ሌት ተቀን ተግተን እንሰራለን ፤ ፈጣሪም ይረዳናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.