በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃን ይዟል።
ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!
በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃን ይዟል።
የዛሬ 12 ዓመት ያቋቋምነው የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ዘንድሮም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ማሳለፍ የቻለ ሲሆን የዚሁ ተምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ጃለላ ግርማ ኩሳ 591.6 ወጤት በማምጣት እንደ ሀገር ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቷል።
በከተማ አስተዳደራችንም የእቴጌ መነን የሴቶችና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 24 ትምህርት ቤቶች ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ ችለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ከሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛው ውጤት 569.1 ያመጣችዉ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኘው ከቦሌ ሱፕር ሆሊ ሴቪየር ት/ቤት ተማሪ መቅደላዊት ሱራፌል ማሞ ነች።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም የተጀመረውን ስትራቴጂ በአግባቡ መተግበር ፣ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሰናስለው መስራት ፣ ወላጆች ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ስራው ስኬት ባለቤት ሆኖ መስራት እንዲሁም ተማሪዎች ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.