ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት" ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ወጣቶችን አበረታተዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው፥ ውድድሩ በአደጉና በበለፀጉ ሀገራት እጅግ ተወዳጅ ስፓርት ሲሆን፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፓር መሰረተ ልመቶችን  የሚፈልግ በመሆኑ  እስከአሁን በአገራችን ሲካሄድ አይስተዋልም፥  ዛሬ ግን በከተማችን በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ምቹ የስፓርት መሰረተ-ልማቶች እውን በመሆናቸዉ አዳዲስ የፓርት አይነቶች እየተካሄዱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል። 

በመቀጠልም፥ ውድድሩ  ወጣቶች ልዩ ተሰጥኦና ችሎታቸዉን የሚዳብሩበት ፣ለስፖርት ቱሪዝም፥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት፣ የከተማችንን ገፅታ የሚቀይር እና ተወዳዳሪነታችን የሚጨምር  ነው ብለዋል። 

በመጨረሻም እንዲህ አይነት ውድድሮች፥ ወጣቱን ታሳቢ ያደረጉ መሠረተ-ልማቶችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንሰራ ያደርገናል፤ ወጣቱም አለማቀፍ የተወዳዳሪነት መንፈስ እንዲያሳድግ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። 

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው አዘጋጆችን “በርቱ” ያሉ ሲሆን፤ ለተወዳዳሪዎችም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.