በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የተደረገው ታላቁ "ዓድዋ ናይት ፋይት" (Adwa Night Fight) የሚክስድ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በታላቅ ስኬት፣ በደመቀ ድባብ እና በሰላም ተጠናቋል!
"ዓድዋ ናይት ፋይት" በአዲስ አበባ ሰማይ ስር የተጻፈ አዲስ የስፖርት ታሪክ!
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የተደረገው ታላቁ "ዓድዋ ናይት ፋይት" (Adwa Night Fight) የሚክስድ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በታላቅ ስኬት፣ በደመቀ ድባብ እና በሰላም ተጠናቋል!
ይህ ታሪካዊ ምሽት የከተማችንን ሁለገብ አቅም፣ የስፖርታዊ ውድድሮች አዲስ እይታን፣ እንዲሁም መዲናችን አዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ታላላቅ የስፖርት ዝግጅቶች የማስተናገድ ብቃቷ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ዳግም ያረጋገጠበት ነበር። ዋና ዋና የስኬት ኩነቶች፦
1. ስማርት እና ዘመናዊ አዲስ አበባ :-የኢትዮጵያዊነት እና የፅናት ምልክት በሆነው በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደው ይህ ውድድር፤ የከተማችንን ዘመናዊነት (Smart City) እና ለትላልቅ አለም አቀፍ ኹነቶች ያላትን ዝግጁነት በግልጽ እና በተግባር አሳይቷል።
2. የተወዳዳሪዎች ድንቅ ብቃት:-ተወዳዳሪዎቻችን ያሳዩት ከፍተኛ የቴክኒክ፣ የፅናት እና የስፖርታዊ ጨዋነት ብቃት የምሽቱን ሳቢነት እና አዛኝነቱን በእጅጉ ጨምሮታል።
3. የስፖርቱ አዲስ ምዕራፍ:- እንደ Mixed Martial Arts (MMA) ያሉ አዳዲስ እና አሳታፊ የስፖርት አይነቶች በሀገራችን እያደጉ መምጣታቸውን እና የወጣቶቻችንን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆናቸውን ማሳያ ነው።
4. የህዝቡ ደማቅ አቀባበል፦ የስፖርት አፍቃሪው ህዝባችን ያሳየው ደማቅ ድጋፍ እና ፍቅር ውድድሩ ልዩ ቀለም እንዲላበስ አድርጎታል።
ይህ ታላቅ ዝግጅት በስኬት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተወዳዳሪዎች፣ አዘጋጆች፣ የስፖርት አፍቃሪዎች እና ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
አዲስ አበባ፣ የአለም አቀፍ ስፖርታዊ ኹነቶች እና የታላላቅ ህልሞች መድረክ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.