ዓለም ዕውቀና የቸረው የአዲስ አበባ የትውልድ ግንባታ ተግባር
ዛሬን በሰው ተኮር ተግባራቶቿ የብዙዎች የከተማው ነዋሪዎቿ እንባ ያበሰችው አዲስ አበባ፤ ነገዋን ብሩህ ለማድረግ ደግሞ በትውልድ ግንባታ ላይ ያልተቆጠቡ ስራዎችን እያከናወነች ነው፡፡
የዛሬ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ ናቸው በሚል መርህ ባለፉት ሶስት ዓመታት አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ የምትመች ምርጧ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ የተሰራው ስራ እና የተገኘው ውጤት ፈርጀ ብዙ ነው፡፡
የሰው ልጅ አእምሮ በህይወት ዘመኑ ከሚያሳየው አጠቃላይ እድገት ውስጥ እጅግ ፈጣኑ እና ወሳኙ ክፍል በመጀመሪያዎቹ የልጅነት ዓመታት ውስጥ የሚከናወን ነው፡፡
የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህፃናት እድገት ማዕከል እና የአለም ጤና ድርጅት ሳይንሳዊ መረጃ እንደሚያሳየው የህፃናት የአዕምሮ ዕድገት አስከ ሶስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ 80 በመቶ እንደሚጠናቀቅ ሲያረጋግጥ፤ ይህ እድገት ከ5- 6 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶ ላይ እንደሚደርስ ሳይንሳዊ ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡
ህፃናት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚያገኙት እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ጥሩ አመጋገብ እና ማነቃቂያ (ጨዋታ፣ ንባብ፣ የንግግር ችሎታ) የወደፊት አእምሯዊ ብቃታቸውን ይወስናል።
በመሆኑም በቀዳማይ ልጅነት መረኃ ግብር ላይ መስራት ለወደፊት ትውልድ ግንባታ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመሰጠት በለፉት ዓመታት ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ በቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብሩ የህፃናት የተቀናጀ የጤና እና የክትትል አገልግሎት በተጨማሪ በህፃናት ማቆያ እና የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ያሉ የህፃናት ማቆያዎች 11 ብቻ ነበሩ ዛሬ 1100 ደርሰዋል፤ 20 የነበሩት የህፃናት መጨወቻዎች አሁን 5 ሺህ ደርሰዋል። ይህ መዋቅራዊ ለውጥ ነው፡፡
ቤተሰቦቻቸው መክፈል ለሚችሉ ህፃናት ብቻ ተትቶ የነበረው የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሁን በአዲስ አበባ ለሁሉም ሆኗል፤ ልጆቻቸው እስኪያድጉ ከስራ ገበታ እርቀው ለኢኮኖሚ ችግር ይጋለጡ የነበሩ እናቶች ዛሬ ላይ ግን በተዘጋጀው የህዝብ የህፃናት ማቆያ ልጆቻቸውን በማስቀመጥ አምራች ወደሚያደርጋቸው የስራ ገበታ ላይ መሰማራት እንዲችሉ አድርጓል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ መራኃ-ግብር በአዲስ አበባ 1.3 ሚሊዮን ህፃናት በመረኃ ግብሩ ታቅፈው ተጠቃሚ እየሆኑ ሲሆን ፕሮግራሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ እምርታዊ ለውጥ እያስመዘገባ ይገኛል፡፡
ዋና መቀመጫው በእንግሊዝ ለንድ የደረገው Act For Early Years ኢኒሼቲቭ በፈረንጆቹ 2023 በይፋ ስራውን የጀመረ ሲሆን መሰረታዊ እንክብካቤ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት የተነፈጉ ከ350 ሚሊዮን በዓለም ላይ የሚገኙ ህፃናትን ችግር እልባት ለመስጠት የተመሰረት ኢንሼቲቭ ነው፡፡
ኢንሼቲቩ በዋናነት የመንግስታት እና ፖሊሲ አውጪዎችን ግንዛቤ በመለወጥ ከጽንሰት እስከ ስድስት ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት ጉዳይ ትኩረት እዲሰጥ ማድረግ ሲሆን ፕሮግራሙ በበርካታ ሀገራት ተግባራዊ ሲደረግ በእነዚህ ዓመታት ውስጥም አዲስ አበባ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ግንባር ቀደም ከተማ ስትባል፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤም በኢንሼቲቩ"የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን" ማዕረግን ተቀዳጅተዋል፡፡
ይህን እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.