የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ስራችን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልናዋጣ አቅደን ነበር።
ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊዮን ብር በላይ ማዋጣት ችለናል። ኢትዮጵያን ሲያኮሩ የኖሩ አትሌቶች፣ ስፖርተኞች እና ደጋፊዎች፣ የዘወትር አገልጋይ የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ለኅሊናም ለአካባቢም ንፅህና የሚቀኙ ከያንያን፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች በቴሌቶኑ ስፍራ በመገኘት ላደረጉት አስተዋጽዎ እነሆ ምስጋና።
በመላው አለም ሆነው በዛሬዋ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶኑ የተሳተፉ ከአርባ ሺህ በላይ ዜጎች ለፅዱ ኢትዮጵያ ያላቸው ምኞት መግለጫ የሆነው አስተዋፅዖ በተግባር በየአካባቢው በሚገነቡ የሕዝብ መፀዳጃዎች ይታወሳል።
ይህ ትውልድ ጀምበር ወጥታ በገባች ቁጥር ለመጪው ትውልድ መስፈንጠሪያ የሚሆን ብሩህ እና ፅኑ መሰረት ደልድሎ ያወርሳል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.