የህብር ቀን! በብዝሀ አብሮነት፣ በህብር ኪነ ጥ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህብር ቀን! በብዝሀ አብሮነት፣ በህብር ኪነ ጥበባዊ ድግስ በአራት ኪሎ ፕላዛ!

የብዝሀነት ድምቀት ፣ የአብሮነት ውበት፣ ህብር መልክ የሚንፀባረቅባት መዲናችን አዲስ አበባ እንደ አበባ ፈክታለች።

የቱሪስት መሸጋገሪያ እንጅ መዳረሻ ያልነበረችው መዲናችን የነዋሪዎቿ ምቹ ለጎብኝዎች ደግሞ ተመራጭ ሆናለች።

በኮሪደር ልማት እና በወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ተምሳሌትነቷን ያሰፋችው አዲስ አበባ ለኪነ ጥበብ ማንሰራራትም ትልቅ አቅም ፈጥራለች።

ከኮሪደር ልማቱ ዘርፈ ብዙ ቱሩፋቶች አንዱ የሆነው የአራት ኪሎ ፕላዛ ጳጉሜን 4 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶችን በድምቀት አስተናግዷል።

በውዲቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር የተጀመረው መርሃ ግብሩ በአካል ጉዳተኞች ፣ በወጣቶች ፣ በታዳጊዎች ህብር ዝማሬ ደምቋል።

በፕሮግራሙ ላይ ለሀገራችን ሰላምና ዕድገት ፣ ለህዝባችን ህብር አብሮነት ምርቃታቸውን ያቀረቡት አረጋውያን፣ ያለፉበትን የህይወት መንገድ በማጣቀስ ትውልዱ የሀገር ፍቅሩን በተግባር ሊተረጉም እንደሚገባ ምክራቸውን ለግሰዋል።

ታዳጊዎች ከአረጋውያን የማይነጥፍ እውቀት የቀሰሙበት፣ ልምድ የሰነቁበት የጭውውት ኘሮግራምም ተካሂዷል።

የብሔር ብሔረሰቦች ህብር ዜማዎች፣ የሰዓሊያን እና የባለ ተሰጥኦ ታዳጊዎች የስዕል ውድድር እንዲሁም የታዳጊ ሴቶች የጥያቄና መልስ ውድድር በአራት ኪሎ ፕላዛ በተዘጋጀው የኪነ ጥበብ ድግስ ተከናውኗል።

ህብር አብሮነትን በሚያጠናክሩ  ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በደመቀው የአራት ኪሎ ፕላዛው የጳጉሜን 2 የህብር ቀን አከባበር፣ በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም የባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀገር ባለውለታ አረጋውያን፣ ታዳጊዎች ፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ተማሪዎች፣ ሰዓሊያን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኦኬስትራ አባላት እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.