«ህብር የወጣቶች ካርኒቫል» በአድዋ ድል መታሰቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

«ህብር የወጣቶች ካርኒቫል» በአድዋ ድል መታሰቢያና በዋና ዋና አደባባዮች በታላቅ ድምቀት ተካሄደ

የህብረ-ብሔራዊ አንድነትንና አብሮነትን እሴቶች የሚያጠናክሩ፣ እንዲሁም የመልካም ምኞት መግለጫ የሆኑ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የቀረቡበት «ህብር የወጣቶች ካርኒቫል» በአድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በመዲናዋ ዋና ዋና አደባባዮችና የልማት ማዕከላት በታላቅ ደስታና ድምቀት ተካሄደ።

በዕለቱ በቀበና ፕላዛ በተካሄደው የካርኒቫል መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ መርሃ-ግብሩ ከህብር ቀን ጋር ተያይዞ የወጣቶችን የጋራ አቅም፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትና አብሮነትን በግልጽ ያሳየ ታላቅ መድረክ ነው ብለዋል።

ም/ቢሮ ሀላፊው አክለውም ወጣቶች በጋራ በመቆም ለሀገራቸው ሰላም፣ እድገትና ልማት አዎንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ያላቸውን ቁርጠኝነት የታየበት ኩነት መሆኑን አብራርተዋል።

በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው የወጣቶች ካርኒቫል ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ በበኩላቸው ወጣቶች የሀገር ግንባታ ዋና ባለቤቶች እንደመሆናቸው መጠን እንዲህ ያሉ የካርኒቫል እና የኪነ-ጥበብ መድረኮች እርስ በእርስ የመቀራረብ፣ ባህልና እሴቶችን የመለዋወጥ እንዲሁም ህብረታዊ ውበትን የማጎልበት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። 

አቶ ክብረአለም አያይዘውም ቢሮው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደርጋቸውን ሰፊ እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ በሜክሲኮ አደባባይ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የቢሮው ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን  የወጣቶች ህብረ-ብሔራዊ አንድነትንና በጎ አቅም ለከተማዋ ሰላምና ልማት ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በካርኒቫሉ ላይ የተሳተፉ በርካታ ወጣቶች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በመዲናዋ በኮሪደር ልማት የተገነቡት ምቹ፣ ጽዱ እና ዘመናዊ የመዝናኛ ቦታዎችና አደባባዮች እንደዚህ ያሉ ትላልቅ ህዝባዊና ባህላዊ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ አዳዲስ ስፍራዎች ወጣቶች በነፃነት ተገናኝተው አብሮነታቸውን፣ ወንድማማችነታቸውንና አንድነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ እድል እንደፈጠሩላቸው ተናግረዋል።

በዕለቱ በአድዋ ድል መታሰቢያ፣ በቀበና ፕላዛ፣ በሜክሲኮ አደባባይ እና በሌሎችም የመዲናዋ አደባባዮች የቀረቡት የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች፣ ባህላዊ ትርኢቶች እና የወጣቶች የፈጠራ ስራዎች ለህብረተሰቡ ልዩ የደስታ ስሜት የፈጠሩ ሲሆን መርሃ-ግብሩ የወጣቶችን በጎ አቅም እና የከተማዋን አዲስ ገጽታ ባጎላ መልኩ  ተጠናቆል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.