ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተገናኝተን መክረናል።
በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።
ውይይታችን ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል።
ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው።
It was a pleasure to meet Prime Minister Anwar Ibrahim of Malaysia on the sidelines of the BRICS Summit and build on the momentum of his historic visit to Addis Ababa in November 2025.
Our discussions focused on expanding investments, tourism, renewable energy partnerships and cooperation in the lead up towards COP32. We also explored opportunities to learn from Malaysia’s experience in industrial parks, productivity, and manufacturing.
Ethiopia and Malaysia share significant potential for a stronger economic partnership, creating new opportunities in investment, technology, skills, and sustainable development.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.