በመዲናችን "መስቀልና ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ዉይይት ተካሔደ
"የኢትዮጵያዉያን የበለፀጉ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካዉያን የሚኮሩበት፤ዓለም የሚታደምበትና የሚደመምበት ልዩ ገፀ-በረከቶች ናቸዉ፡፡" ተሳታፊዎች
በመዲናችን "መስቀልና ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ዉይይት ተካሔደ
በመዲናችን በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በመዲናችን "መስቀልና ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ዉይይት ዛሬ ተካሄዷል፡፡
በዉይይት መድረኩም "መስቀልና ኢሬቻ" የኢትዮጵያዉያን የበለፀጉ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካዉያን የሚኮሩበት፤ዓለም የሚታደምበትና የሚደመምበት ልዩ ገፀ-በረከቶች መሆናቸዉንና ለከተማችን ብሎም ለሃገራችን ፋይዳቸዉ ዘርፈ-ብዙ ነዉ ተብሏል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም የመስቀል በዓል የእውነት፣የመስዋዕትነት እና የድል ምልክት ሲሆን፤ የኢሬቻ በዓል ደግሞ ለፈጣሪ (ዋቃ) የሚቀርብ የምስጋና፣ የተፈጥሮን እንክብካቤ እና የሰላም ትምህርት ያዘለ ሃገርንና ትዉልድን ወደሻለ ከፍታ በህብር የሚያሻግሩ የጋራ ሀብት መሆናቸዉ የዉይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
አክለዉም በዓላቱን ለዓለም ህዝብ ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ቅርሶቹ በትውልድ መካከል እንዲተላለፉ እና የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚያስችል ትልቅ ማዕቀፍ በመሆኑ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ጉዞአችን ሁላችንም አንድ ሆነን ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እና ሰላማዊ ሆኖ ተከብረው እንዲጠናቀቁ ታሪካዊ ሃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በዓላቱን በተፈጠሩ ምቹ እድሎች በመዲናችን ስናከብር ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ገቢ እድገት እና ለአገልግሎት ሰጪው ዘርፍ ጉልህ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይፈጥራል በማለት ዝግጁነታቸዉን ጭምር አረጋግጠዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.