በአራት ወር ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “
በአራት ወር ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል?
👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች
👉 በአራት ወራት ዉስጥ የተገነቡ 960 ቤቶች
👉 ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች
👉 በውስጡ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣
👉 የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥
👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ
👉 ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች
👉 ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤
👉 እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ: በአስከፊ የእሳት አደጋ የተጎዳ አካባቢ ነበር
👉 “መርካቶ የበጎነት መንደር “ አካባቢዉን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸውን እንደ ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ ያሉ ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.