በዛሬው ውሏችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ልምድ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በዛሬው ውሏችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ልምድ ለመቅሰም ወደ መዲናችን ለመጡ መሪዎች የትውልድ ግንባታ ስራችን የሆነው የህጻናት መዋያዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን አስጎብኝተናል::

ዛሬ አብዝተን የምንዘራው መልካም ዘር ነገ የተትረፈረፈ መልካም ፍሬን እንደሚሰጠን በማመን በከተማችን 597 የህጻናት መዋያዎችን በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ፣ በግል እና በመንግስት ተቋማት ውስጥ የገነባን ሲሆን በነዚህ ማቆያዎች ለህጻናቱ የተመጣጠነ ምግብ ፣ የሞግዚት አገልግሎት ፣ የጤና ክትትል ፣ ትምህርት በጨዋታ መስጠት ፣ የእናቶች ምክር አገልግሎት እንዲሁም ህፃናት የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው ልዩ ክትትል ይደረግላቸዋል::

አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ የማድረግ ስራችን እውቅናን አግኝቶ ለሌሎች ልምድ የሚያካፍል ደረጃ ላይ በመድረሱ ደስታ የሚሰማን ሲሆን በቀጣይ የህጻናት መዋያዎችን 1000 የመጫወቻ ቦታዎችን ደግሞ 12 ሺሕ ለማድረስ በርትተን እንስራ::

ይህን መልካም ስራ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ላስተባበራችሁ ፣ ለመራችሁ እና በቅርበት ከእኛ ጋር ለሰራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎች ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.