አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው

ለመስቀል እና ለኢሬቻ በዓላት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ለሚገኙ ቱሪስቶችና እንግዶች ደማቅ አቀባበል እየተደረገ ነው፡፡

በየአመቱ በሚከበሩት የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙ ሲሆን በዓላቱ የሀገርን መልካም ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ሁነኛ የቱሪዝም የገቢ ምንጭ በመሆን የከተማዋን ኢኮኖሚ እየደገፈ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ለቱሪስቶች እና እንግዶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.