በመዲናችን የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸዉ መንገዶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸዉ መንገዶችና አደባባዮች የፅዳት ንቅናቄ መረሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ ታላቁን የመስቀል ደመራ በዓል በአብሮነት፤በሰላም እና በድምቀት ለማክበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሰፊዉ ሲካሄዱ ቆይተዋል፤እየተከናወኑም ይገኛሉ፡፡ 

ከእነዚህ ዝግጅቶች አንዱ በሆነዉ እና እየተካሄደ ባለዉ የፅዳት ንቅናቄ መርሃ ግብር ላይ  የሁሉም ሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግሥት አመራሮችና የሥራ ሃላፊዎችና ፣የፅዳት አምባሳደሮች እንዲሁም በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት መገለጫ እንደ መሆኑ መጠን፣ ቦታዎቹ ንፁህና ለዕይታ የሚስቡ በተለይም ለበዓሉ እንግዶችና አክባሪዎች ምቹና ማራኪ እንዲሆኑ ትኩረት በመስጠት የተደረገው ጥረት የህብረተሰቡን የባለቤትነት ስሜትና በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

የፅዳት መርሃ ግብሮቹን ጨምሮ መዲናችን አዲስ አበባ ለበዓሉ የሰጠችዉ ልዮ ትኩረት የከተመዋን ገፅታ ይበልጥ ለማጉላት እና ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትዉፊቶችን ጠብቃ ለትዉልድ ለማስተላለፍ  ዝግጁ መሆኗን ያሳያል ተብሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.